Fana: At a Speed of Life!

“የምሥራቅ ኢትዮጵያ ፈጥኖ ደራሽ ማዕከል” ከ676 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከ676 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ “የምሥራቅ ኢትዮጵያ ፈጥኖ ደራሽ ማዕከል” በድሬዳዋ ከተማ ሊያስገነባ ነው፡፡

የኮንትራት ውል ሥምምነቱን ከመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ጋር መፈራረሙን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ኅብረት ድርጅት ፕሬዚዳንት እና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ÷ የምሥራቅ ኢትዮጵያን ሠላምና ደኅንነት ለማጠናከርና እያደገ የመጣውን የፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ኃይል አደራጅቶ ለመምራት ማዕከሉን በድሬዳዋ ከተማ ማስገንባት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።

መንግስት ለፖሊስ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ6 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የፕሮጀክቶች ግንባታ ተፈቅዶ እየተሠራ መሆኑንም ገልፀዋል።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ሰሎሞን ደመቀ በበኩላቸው ÷ ለፕሮጀክቱ ግንባታ በቂ የሰው ኃይልና ግብዓት መኖሩን አንስተዋል፡፡

ጥራቱን በጠበቀ ደረጃ ከተቀመጠው ጊዜ በፊት አጠናቀው እንደሚያስረክቡም ነው የገለጹት።

የፕሮጀክቱ ግንባታ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅም ነው የገለጹት ዋና ሥራ አስፈፃሚው።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በቀጣይ የፖሊስ ሠራዊቱን የመኖሪያ ካምፕ ችግር ለመቅረፍ የጀመራቸውን የፕሮጀክቶች ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.