Fana: At a Speed of Life!

ሁለተኛው ሀገር አቀፍ የማህበራዊ ጥበቃ ኮንፈረንስ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው ዙር ሀገር አቀፍ የማህበራዊ ጥበቃ ኮንፈረንስ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ መካሄድ ጀመረ፡፡

በኮንፈረንሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ ከሀገር ውስጥና ከተለያዩ የውጭ ሀገራት የተውጣጡ ባለድርሻና አጋር አካላት እየተሳተፉ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ኮንፈረንሱ “ማህበራዊ ጥበቃ ለሀገር ግንባታ በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል ከግንቦት 15 እስከ 16 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)÷ኮንፈረንሱ በባለድርሻ አካላት መካከል ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ለማጠናከርና ሁሉም ለስኬታማ ትግበራ የድርሻውን እንዲወጣ ለማስቻል የበኩሉን እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.