Fana: At a Speed of Life!

የጂቡቲ፣ የጋቦን፣ የዚምባብዌ እና የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንቶች አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጂቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ፣ የጋቦን ፕሬዚዳንት ብሪሴ ኦሊጉዊ ንጉዌማ እና የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ በ39ኛው የኅብረቱ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቶቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በተመሳሳይ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፋውስቲን ቱዋዴራ በመሪዎች ጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በተጨማሪም የአልጄሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲፊ ጋሪብ፣ የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ፣ የሲሼልስ ምክትል ፕሬዚዳንት ሰባስቲያን ፒሌ፣ የኮቲዲቯር ምክትል ፕሬዚዳንት ቲሞኮ ሜይሌት ኮኔ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

መሪዎቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

39ኛው የኅብረቱ የመሪዎች ጉባዔ “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፥ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.