በሶማሌ ክልል ሀገራዊ የግብር ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ሀገራዊ የግብር እና የጉምሩክ ሕግ-ተገዥነት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ ግብርና የታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና አሰጣጥ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡
በመርሐ ግብሩ የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አይናለም ንጉሴና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር ሀገራዊ የታክስ እና የጉምሩክ ሕግ-ተገዥነት ንቅናቄ”ግብር፤ ለሀገር ክብር” በሚል መሪ ሀሳብ አቅዶ እየሰራ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡