511 ማህተሞችን በመጠቀም ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጁ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
አቶ አሻግሬ በለጠ አለሙ እና ግብረአበሮቹ በአራዳ ክፍለ ከተማ 511 ማህተሞችን በመጠቀም ሃሰተኛ የመንግስት ተቋማት ሰነዶችን ሲያዘጋጁ ነው በቁጥጥር ሥር የዋሉት።
ግለሰቦቹ ከ1 ሺህ 500 እስከ 4 ሺህ 500 ብር በማስከፈል ሃሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት የወንጀል ተግባር ሲፈፅሙ እንደነበር ተገልጿል፡፡
ያዘጋጇቸው የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ሀሰተኛ ሰነዶችም በኢግዚቢትነት መያዛቸውን ከአዲስ በባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡