Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ኅብረት የብዝኀ ሕይወት ጥበቃ ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ኅብረት የብዝኀ ሕይወት ጥበቃ ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የተዘጋጀው ስብሰባ በተለይ የአፍሪካ፣ የካሪቢያንና የፓስፊክ የብዝኀ ሕይወት ዓለም አቀፍ ሥምምነት፣ የኮፕ-15 የተመድ የብዝኀ ሕይወት ስብሰባና በ19ኛው የንግድ እንቅስቃሴ ምክንያት እንስሳትና ዕጽዋት ላይ ጉዳት ላለማድረስ የተደረገ ስምምነት ስብሰባ ውጤቶች ትግበራ ላይ ያተኮረ ነው።

የአፍሪካ ኅብረት የዘላቂ አካባቢ ጥበቃና ብሉ ኢኮኖሚ ዳይሬክተር ሀርሰን ኒያምቢ÷ ብዝኀ ሕይወት በአፍሪካ በቱሪዝም፣ መድሐኒት፣ ኢንዱስትሪ እና በንግዱ ዘርፍ ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።

ሕገ-ወጥ ንግድ እና የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ በብዝኀ ሕይወት ጥበቃ ውስጥ የሚስተዋሉ ችግሮች መሆናቸው በመድረኩ ተነስቷል።

በመሆኑም የዓለም የብዝኀ ሕይወት ስብሰባ ውጤቶችንና ስምምነቶችን ተቀናጅቶ መተግበር እንደሚያስፈልግ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የቴክኖሎጂ፣ አየር ንብረት ለውጥና የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ ዳይሬክተር ጂን ፓል ÷ ሀገራት ቀጣይነት ያለው ብዝኀ ሕይወት እንዲኖር እያከናወኑ ያለውን ተግባር ያነሱ ሲሆን ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በምሳሌነት አንስተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.