Fana: At a Speed of Life!

አረንጓዴ ዐሻራ ለትውልድ የሚተርፍ ቅርስ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አረንጓዴ ዐሻራ ለትውልድ የሚተርፍ ቅርስ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷’ነገን ዛሬ እንትከል‘! ይህ ዛሬ ለምንጀምረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የሁለተኛው ምዕራፍ ጅማሮ መሪ ሐሳብ ነው ብለዋል፡፡

25 ቢሊየን ችግኞችን የተከልንበት የመጀመሪያ ምዕራፍ ተሳክቷልም ሲሉ ገልጸዋል።

በሁለተኛው ዙር ደግሞ ኢትዮጵያ 25 ቢሊየን ችግኞችን ትተክላለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷አረንጓዴ ዐሻራ ለትውልድ የሚተርፍ ቅርስ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

የአየር ንብረት ለውጥን እና የአካባቢ መራቆትን ለመቋቋም የወጠንነው ሀገር በቀል አካሄዳችን ነው ብለዋል።

የሥራ ዕድል ለመፍጠር አንዱ መንገድ መሆኑን ጠቅሰው÷ ለምግብ የሚውሉ ዕጽዋትን በመትከል የምግብ ዋስትናችንን የምናረጋግጥበት አንዱ መንገድ ነውም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.