ለጎረቤት ሀገራት ከቀረበ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከ83 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት ዓመት 10 ወራት ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ካቀረበችው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከ83 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን እንደገለጹት÷ በበጀት ዓመቱ 10 ወራት ከሀገር ውስጥ የኃይል ሽያጭ ከ14 ቢሊየን ብር በላይ እንዲሁም ለጎረቤት ሀገራት ከተሸጠው የኤሌክትሪክ ኃይል ከ83 ሚሊየን ዶላር በላይ ተገኝቷል፡፡
ጅቡቲ፣ ኬንያ እና ሱዳን የኤሌክትሪክ የኃይል ሽያጭ የተደረገባቸው ሀገራት መሆናቸውን ነው ዳይሬክተሩ ያመለከቱት።
ኢትዮጵያ ከጅቡቲ እና ሱዳን በተጨማሪ በሕዳር ወር 2015 ዓ.ም ለኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል መሸጥ መጀመሯ የሚታወስ ነው።
የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጩ ቀጣናውን በኢኮኖሚ የማስተሳሰር እቅድ አካል እንደሆነም ይታወቃል።
በበጀት ዓመቱ 10 ወራት ከመነጨው ኃይል ውስጥ 12 ሺህ 126 ጊጋ ዋት ሽያጭ ተከናውኗል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ይህም በእቅድ ከተያዘው ጋር ሲነጻጸር አፈጻጸሙ 85 በመቶ መሆኑንና ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም በ26 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ጠቁመዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!