Fana: At a Speed of Life!

በጃፖን የሚገኙ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ለመሳተፍ ፍላጎታቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፖን የመንግስት እና የግል ኩባንያ ኃላፊዎች  በኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሳተፍ ያላቸውን ፍላጎት ገለጹ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ከጃፓን የመንግስት እና የግል ኩባንያ የሥራ ኃላፊዎች በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንት ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ የኢትዮጵያ መንግስት ልማትንና ኢንቨስትመንትን ለማፋጠን ያደረጋቸውን የፖሊሲ፣ የሕግና ተቋማዊ ሪፎርሞችን ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት ዕድል ተጠቅመው የጃፓን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ መጋበዛቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የጃፖን የመንግስት እና የግል ኩባንያ ኃላፊዎች  በበኩላቸው ÷  በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ በኢትዮጵያ ለመሳተፍ ያላቸውን ፍላጎት ገልፀዋል።

በጃፓን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርም÷ ኩባንያዎቹ በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ሙሉ ድጋፍ  እንደሚሰጧ ቸው አረጋግጠውላቸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.