Fana: At a Speed of Life!

የማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭትን በተመለከተ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብርና ሚኒስቴር በ2015/16 የምርት ዘመን የማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭት ላይ ከክልል ባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው።

በመድረኩ የኦሮሚያ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮዎች ማዳበሪያ የሚያጓጓዙ ትራንስፖርት ሰጪዎች እንዲሁም ዩኒየኖች እየተሳተፉ ነው።

ዩኒየኖቹ ለአርሶ አደሩ የዘር ወቅት እያለፈበት ቢሆንም በቂ ማዳበሪያ እያቀረቡ እንዳልሆነ ፤በዚህም በምርት መቀነስ ስጋት ላይ እንደሚገኙ አንስተዋል።

እናቀርባለን ብለው ካሰቡት ማዳበሪያ በጣም አነስተኛ ቁጥር እንዳገኙና ዘርፉ ችግር እንደተደቀነበትም ነው የጠቆሙት።

በኢትዮጵያ ምርታማነታቸው ከፍተኛ የሆኑ አካባቢዎችም የምርትና ምርታማነት ስጋት ላይ መሆናቸውም ተነስቷል።

የአርሶ አደሮች የግብርና ፍላጎት እያደገ መምጣት፣ የፀጥታ ችግር፣ በማዳበሪያ ላይ የተደረገው ድጎማ በጊዜ አለመተግበሩና የማጓጓዝ ችግሮች በተፈለገው ልክ እንዳይገባ አድርጓል ተብሏል።

በተጨማሪም ÷ምንጩ በትክክል የማይታወቅ የማዳበሪያ ህገወጥ ዝውውርም ለእጥረቱ ምክንያት ሆኗል ብለዋል ተሳታፊዎቹ።

የቁጥጥርና ክትትል ማነስ፣ የመረጃ አያያዝና ሪፖርት ችግር፣ የተያዙ ህገ ወጦች ላይ ተገቢው እርምጃ ያለመውሰድ ችግሮች እንዳሉም ዩኒየኖችና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ማህበራት ኤጀንሲ ባቀረቧቸው ሰነዶች ተመላክቷል።

በአፈወርቅ እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.