የመከላከያ ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች የጤና አውደ-ርዕይን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ ያለውን የጤና አውደ-ርዕይ ጎበኙ።
በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀው ብሔራዊ የጤና ኤግዚቢሽን ከሰኔ 13 ጀምሮ በተለያዩ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች የተጎበኙ ሲሆን÷ በዛሬው ዕለትም የመከላከያ ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች ጎብኝተውታል።
በአውደ ርዕዩ ኢትዮጵያ ከአገር በቀል ዕውቀት እስከ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የህክምና ቴክኖሎጂዎች የደረሰችበት የጤና እመርታም ቀርቦበታል።
በጉብኝቱ የመከላከያ ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች በአውደ-ርዕዩ የቀረቡ በጤናው ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ተመልከተዋል።
በጉብኝቱ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ እያከናወነች ስላለችው ስራዎችና የተገኙ ውጤቶች እንዲሁም የጤናው ዘርፍ የደረሰበት የዕድገት ደረጃ ላይ ገለጻ የተደረገላቸው መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።