Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች የጤና አውደ-ርዕይን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ ያለውን የጤና አውደ-ርዕይ ጎበኙ።

በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀው ብሔራዊ የጤና ኤግዚቢሽን ከሰኔ 13 ጀምሮ በተለያዩ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች የተጎበኙ ሲሆን÷ በዛሬው ዕለትም የመከላከያ ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች ጎብኝተውታል።

በአውደ ርዕዩ ኢትዮጵያ ከአገር በቀል ዕውቀት እስከ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የህክምና ቴክኖሎጂዎች የደረሰችበት የጤና እመርታም ቀርቦበታል።

በጉብኝቱ የመከላከያ ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች በአውደ-ርዕዩ የቀረቡ በጤናው ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን  ተመልከተዋል።

በጉብኝቱ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ እያከናወነች ስላለችው ስራዎችና የተገኙ ውጤቶች እንዲሁም የጤናው ዘርፍ የደረሰበት የዕድገት ደረጃ ላይ ገለጻ የተደረገላቸው መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.