በአማራ ክልል አሁናዊና ቀጣይ ጸጥታ ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል አጠቃላይ አሁናዊ እና ቀጣይ የጸጥታ ሁኔታ ላይ ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት ጋር ምክክር ተካሂዷል።
በመድረኩ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊን ጨምሮ ከዞን እስከ ክልል ያሉ ከፍተኛ የክልሉ የፖሊስ አመራሮች፣ የክልሉ የአድማ መከላከል ሃላፊዎች፣ የፌዴራል ፓሊስና የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በምክክር መድረኩ የክልሉን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት መደረጉን የክልሉ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡