Fana: At a Speed of Life!

የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓል “ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።
በበዓሉ አከባበር ላይ አባ ገዳዎች፣ አባ መልካዎች፣ አባ ሙዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎችና ወጣቶችን ጨምሮ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችና ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የመጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል፡፡
በተጨማሪም የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ልዑካን እና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች በበዓሉ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ የክረምቱን መጠናቀቅ ተከትሎ ለፈጣሪ ምሥጋና የሚያቀርብበትና መጪው ዘመን መልካም እንዲሆን የሚለምንበት በዓል ነው፡፡
የበዓሉ ታዳሚዎችም የኦሮሞ ሕዝብን ባህል በሚያንጸባርቁ አልባሳትና ጭፈራዎች ታጅበው በድምቀት እያከበሩ ይገኛሉ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.