Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለአርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ‘የሸገር’እና ‘ገበታ ለሀገር’ የቱሪዝም ዘርፍ የልማት ሥራዎች በአብዛኛው ተጠናቅቀዋል ብለዋል።

ይሄን ተከትሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ ስምንት የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማልማት የ‘ገበታ ለትውልድ’ ሐሳባችንን ገፍተንበታል ነው ያሉት።

የአርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት በ120 ሄክታር መሬት ላይ የአባያ ሐይቅን እያየ በሚያማምር ቦታ ላይ እንዲገነባ የመሠረት ድንጋይ ማስቀመጣቸውንም አንስተዋል፡፡

በዓመት ከመንፈቅ ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቀው ይህ ፕሮጀክት 1 ነጥብ 3 ትሪሊየን ዶላር የሚሸፍነውን ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ዘርፍ ገቢን ተቋዳሽ እንድንሆን ያደርገናል ብለዋል፡፡

“ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ ሀብታችንን በመጠቀም ሀብት የማፍራት ጅምሮችን በማስፋፋት፣ የብልጽግና ጉዟችንን ለማሳካት እንተጋለን” ሲሉም ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.