Fana: At a Speed of Life!

በጅግጅጋ ከተማ በእሳት አደጋ ከ900 በላይ ሱቆች ወደሙ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ትናንት ሌሊት በተከሰተ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።

 

በጅግጅጋ ከተማ ‘ታይዋን’ ተብሎ በሚጠራው የገበያ ማእከል ትናንት ሌሊት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የተከሰተው ከፍተኛ የእሳት አደጋ በገበያው በሚገኙ የንግድ ሱቆችና በንብረት ላይ ከፍተኛ አደጋ አድርሷል።

 

እሳቱን ለመቆጣጠር የክልሉ የእሳት አደጋ ማጥፊያ ግብረ ሀይልና ከሐርጌሳ ከተማ የተላከለ የእሳት አደጋ አጥፊ ቡድን የእሳት አደጋውን ለማጥፋት ባደረጉት ርብርብ እሳት አደጋውን መቆጣጠር መቻሉን የክልሉ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል።

 

በእሳት አደጋው ሳቢያ 932 ሱቆች ሲወድሙ የደረሰውን ጉዳት የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱም ነው የተገለጸው።

 

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አያን አብዲን ጨምሮ የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የእሳት አደጋው ያደረሰውን ጉዳት ተመልክተዋል።

 

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ በእሳት አደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ነዋሪዎች የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው መንግስት በሁሉም ነገር ለተጎጂዎቹ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.