ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በጅማ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ሒደትን ጎበኙ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመራቂ ተማሪዎችን የመውጫ ፈተና አሰጣጥ ሒደት ተመልክተዋል፡፡
ሚኒስትሩ በፈተና ክፍሎች ተዘዋውረው ሒደቱን በመመልከት ተፈታኞቹን፣ ተቆጣጣሪዎችን እና አስተባባሪዎችን አበረታተዋል፡፡
የቅንጅት እና አፈጻጸም ሒደቱ እስካሁን ጠንካራ መሆኑን ጠቁመው÷በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል።
ማየት ለተሳናቸው የመውጫ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በሒደቱ ውስጥ እየተደረገ ያለውን ድጋፍ ማድነቃቸውንም የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል፡፡
የ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በዛሬው ዕለት መሰጠት መጀመሩ ይታወቃል፡፡