ቻይና ዋንግ ዪን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርጋ ሾመች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ዋንግ ዪን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርጋ መሾሟን ይፋ አደረገች።
የቻይና መንግስት ዋንግ ዪን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርጎ የሾመው በኪን ጋንግ ምትክ ነው።
የቻይና ከፍተኛ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ዛሬ በጠራው ስብሰባ ዋንግ ዪን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርጎ ለመሾም ድምጽ መስጠቱን ቻይና ፒፕልስ ዴይሊ ዘግቧል።
አሁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ዋንግ ዪ ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት አድርገው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዲሁም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር መምከራቸው ይታወቃል።
በዋንግ ዪ የተመራው ልዑክ በሁለትዮሽና እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ማድረጉ ይታወሳል።