Fana: At a Speed of Life!

የሚኒስቴሩ አመራሮችና ሰራተኞች በጎዴ ከተማ አረንጓዴ አሻራ አኖሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በጎዴ ከተማ መናፈሻ ቦታ የተለያዩ 5 ሺህ ችግኞች በመትከል አረንጓዴ አሻራ አኖሩ።

በመርሃ ግብሩ ላይ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር  አይሻ መሀመድ (ኢ/ር) ጨምሮ የሚኒስቴሩ እና የሱማሌ ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

በተጨማሪም ሚኒስቴሩ በጎዴ ከተማ ለሚኖሩ 500 የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ድጋፉን ሚኒስትሯ ለተማሪዎቹ አስረክበዋል።

በዚህም ለእያንዳንዱ ተማሪ አንድ ደርዘን ደብተር፣ ቦርሳና ለዓመት በቂ የሆነ እስክርብቶና እርሳስ መሰጠቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።

ሚኒስቴሩ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከሚከናወኑት ተግባራት መካከል በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ በጎዴ ከተማ ለሚኖሩ 20 አቅመ ደካማ ቤተሰቦች በ3 ነጥብ 2 ሄክታር መሬት ላይ የእስማርት መኖሪያ ቤት መንደር ለመገንባት ትናንት የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጡ ይታወቃል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.