Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞ የአሜሪካ ፖሊስ አባል በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ተፈረደበት

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የአሜሪካ ፖሊስ አባል ቱው ታኦ በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ አራት ዓመት ከዘጠኝ ወር እስራት ተፈርዶበታል፡፡

የጆርጅ ፍሎይድ ግድያን ተከትሎ በፈረንጆቹ 2020 በአሜሪከ እና በዓለም ዙሪያ በዘረኝነት ላይ ፍትህ የሚጠይቅ ከፍተኛ ተቃውሞ ተስተናግዷል፡፡

በፍሎይድ ግድያ በፍርድ ቤት የተከሰሰው የቀድሞ የሚኒያፖሊስ የፖሊስ አባል ቱው ታኦ በትናንትናው ዕለት አራት ዓመት ከዘጠኝ ወር እስራት ተፈርዶበታል።

ታኦ በፈረንጆቹ ግንቦት 25 ቀን 2020 በሰሜናዊ ሚኒሶታ ግዛት ሌላኛው የቀድሞ የፖሊስ መኮንን ዴሪክ ቻውቪን በፍሎይድ አንገት ላይ በጉልበቱ ቆሞበት ሳለ የተሰበሰቡ ሰዎችን መከላከሉን ማመኑ ተገልጿል።

ታኦ ስልጠና የወሰደ በመሆኑ የህክምና እርዳታ አለመስጠትን ጨምሮ በስፍራው የተሰበሰቡ ሰዎች ወንጀሉን ሲፈፅሙ ወደነበሩ ባልደረቦቹ እንዳይጠጉ በማድረግ የፈፀመው ድርጊት በግድያ ተባባሪነት ወንጀለኛ እንዳሰኘውም የአልጀዚራ ዘገባ አመላክቷል፡፡

ሌላኛው የፖሊስ መኮንን ዴሪክ ቻውቪን ከጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ጋር በተያያዘ በፈረንጆቹ ሐምሌ 7 ቀን 2022 የተበዳይን ህዝባዊ መብት በመጣስ ወንጀል የ21 ዓመት እስራት እንደተፈረደበት ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.