Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ የልማት ትብብሩን እንዲያጠናክር ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕዝቡ እና ባለሃብቶች የልማት ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ጥሪ አቀረቡ፡፡

ም/ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ (ዶ/ር ኢ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የክረምት በጎ ሥራዎች አካል የሆነውን የአቅመ ደካሞችና አረጋውያን ቤት ዕድሳት ማስጀመራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ለሀገር አስተዋጽኦ አበርክተው ዛሬ አቅም ያጠራቸውን ወገኖች መደገፍ ይገባል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

“ሁሉም የመንግሥት ተቋማት በሚሠሩበት አካባቢ ከሚገኘው ማኅበረሰብ ጋር በመቀናጀት ዐሻራቸውን እንዲያሳርፉ በተግባባነው መሠረት ሥራዎች ተጀምረዋል” ነው ያሉት፡፡

የትምህር ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል በልዩ ትኩረት እየተመራ መሆኑን ጠቁመው÷ ከኅብረተሰቡና ባለሃብቱ በኩል እየተሰጡ ያሉ ድጋፎችም አበረታች መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በትምህርት ቤቶች ደረጃ ማሻሻል፣ በከተማ ልማት፣ በመንገድና ድልድይ ግንባታ እየታየ ያለው የማኅበረሰብ ተሳትፎ÷ ለልማት ትልቁ የበጀት፣ የእውቀትና የትብብር ምንጭ ስለሆነ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.