Fana: At a Speed of Life!

የረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ በሙሉ አቅሙ ሃይል ማመንጨት ይጀምራል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ በሙሉ አቅሙ ዳግም የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡

የኃይል ማመንጫው ስራ አስኪያጅ ብሩክ ኤባ እንዳሉት÷ ኃይል ማመንጫው በተርባይን ላይ ባጋጠመው ችግር ከጥር ወር 2014 ዓ.ም ጀምሮ የኤሌክትሪክ ኃይል ሳያመርት ቆይቷል።

ከግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተርባይኑ ተጠግኖ ወደ ስራ መግባቱን ጠቅሰው÷ በዚህም 12 ነጥብ 5 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት መቻሉን አስረድተዋል፡፡

የሚመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይልም ከግንቦት 15 ቀን ጀምሮ ወደ ብሔራዊ ቋት እየገባ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ኃይል ማመንጫው አሁን ላይ በአንድ ቦይለር (ቆሻሻ ማቃጠያ) በግማሽ አቅሙ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው÷ ሁለተኛውን ቦይለር ጠግኖ ወደስራ ለማስገባት መለዋወጫ ታዞ እየተጠበቀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሁለት ወር ውስጥ በመረከብ ቦይለሩ ተጠግኖ ኃይል ማመንጫው በሙሉ አቅሙ ያመርታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።

ኃይል ማመንጫው በሙሉ አቅሙ ሲያመርትም 25 ሜጋዋት ኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚያመጭ ነው የገለጹት፡፡

በቀጣይም ከመለዋወጫ ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ስምምነት መደረጉን ተናግረዋል።

ጣቢያው የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት ባሻገር በመዲናዋ በአማካይ በቀን ከሚሰበሰበው 2 ሺህ 500 ቶን በላይ ደረቅ ቆሻሻ ውስጥ÷ 1 ሺህ 280 ቶን ያህሉን የማቃጠል አቅም አለው ነው ያሉት፡፡

አሁን በአንድ ቦይለር 640 ቶን ቆሻሻ በማቃጠል ለከተማዋ ፅዳት አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.