Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በሕገ ወጥ የተያዘ ከ280 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ መሬት ማስመለስ መቻሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሕገ ወጥ መንገድ ተይዞ የነበረ ከ280 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ የመንግስት መሬት ማስመለስ መቻሉን የከተማዋ ፍትሕ ቢሮ አስታውቋል፡፡

በቢሮው የሕግ ክትትል ዘርፍ ም/ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ እንደገለጹት÷በመዲናዋ ከመሬት ነክ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ  ሕገ ወጥ ተግባራትን ለመቅረፍ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ቢሮው ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በቅንጅት እና በትብብር እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በመዲናዋ በሕገ ወጥ መንገድ የተያዙ መሬቶችን በፍርድ ቤት ክርክር  ሕጋዊ እልባት ለማሰጠትም በትኩረት መሰራቱን ነው የተናገሩት፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመትም በሕገ ወጥ መንገድ ተይዞ የነበረ ከ280 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ የመንግስት መሬት ማስመለስ መቻሉን አብራርተዋል፡፡

የተመለሰው መሬትም  መንግስት ለሚሰራቸው  የልማት ፕሮጄክቶች እንዲውል መደረጉን አቶ ተስፋዬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡

 

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.