የኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ቦታዎች ከአሸባሪው ሸኔ ነፃ መሆናቸው ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪው ሸኔ ቡድን አባላት በስፋት ሲንቀሳቀስባቸው የነበሩ የኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ከቡድኑ የሽብር እንቅስቃሴ ነፃ መሆናቸውን ዘመቻውን የሚመሩ ከፍተኛ የሰራዊቱ መኮንኖች ተናገሩ፡፡
ቡድኑ ህብረተሰቡን ለመዝረፍ እና የትራንስፖርት መስመሮችን ለመዝጋት የሚጠቀምባቸው እንዲሁም ለሽብር ስራው ምቹ የነበሩ ቦታዎች ነፃ ማድረግ መቻሉን ነው ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮች ያስታወቁት፡፡
የዘመቻው የከባድ መሳሪያ ምድብተኞች በበኩላቸው÷ በሸኔ ላይ እየተወሰደ በሚገኘው እርምጃ ኃላፊነታቸውን በብቃት እየተወጡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የሚሰጣቸውን ማንኛውም ተልዕኮ በከፍተኛ ሞራል እና ተነሳሽነት በመፈፀም ላይ መሆናቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!