ሰሜን ኮሪያ ጠላቶቿን ለማሥፈራራት ያለመ ክሩዝ ሚሳኤል አስወነጨፈች
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ “ጠላቶቼን ለማሥፈራራት” በሚል በምሥለ-ታክቲካል የኒውክሌር ጥቃት የታገዘ ልምምድ ማድረጓ ተሰምቷል፡፡
በልምምዱም ወቅት የኒውክሌር አረር የተሸከሙ 2 የረጅም ርቀት ክሩዝ ሚሳኤሎችን ወደ ምዕራብ አቅጣጫ የውሃ አካላት ማስወንጨፏ ተገልጿል፡፡
በአንጻሩ የደቡብ ኮሪያ የጦር አዛዦች ልምምዱ በኮሪያ ልሳነ- ምድር ያለውን ሠላም የሚያደፈርስ የትንኮሳ ተግባር ነው ሲሉ መኮነናቸውን ሲ ጂቲ ኤን ዘግቧል፡፡
ሰሜን ኮሪያ ልምምዱን ያደረገችው አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ “ኡልቺ ፍሪደም ሺልድ” በሚል ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖችን ያሳተፉ የ11 ቀናት ጥምር “ዓመታዊ የክረምት ልምምድ” ማካሄዳቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡