በመዲናዋ ለፀጥታ አካላት የእውቅና መስጠት መርሐ- ግብር ተከናወነ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ለፀጥታ አካላት የእውቅና መስጠት መርሐ- ግብር ተከናወነ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ጳጉሜን 2 – የመስዕዋትነት ቀንን በማስመልከት መልዕክት አስተላፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም፥ የመዲናዋን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በታማኝነትና በቅንነት ሲያገለግሉ የህይወትና የአካል መስዋዕትነት ለከፈሉ የፀጥታ አካላት የእውቅና መርሐ- ግብር መከናወኑን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ በብዙ መስዋዕትነት የጸናች ሀገር ናት ሲሉም ገልጸዋል።
አክለው እንዳሉትም፥ ለራሳችሁ ህይወት ሳትሰስቱ ለሀገራችሁ ክብርና ለህዝባችሁ ሰላምና ደህንነት መስዋዕት በመሆን ዋጋ ለከፈላችሁ ሁሉ በሰላም ወጥተን መግባታችን የእናንተ የመስዋዕትነት ውጤት ነውና ኢትዮጵያ ታመሰግናችኋለች ብለዋል::
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!