የመስቀል ደመራ በዓል ዝግጅት
አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የመስቀል ደመራ በዓልን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ተደርጓል አለ።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዓሉ በስኬት እንዲከናወን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች ጋር ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ ወቅት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እንዳሉት፤ ከሃይማኖት መሪዎች ጋር ተገናኝቶ መወያየቱ በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ ሁሉም የየድርሻውን እንዲወጣ ያስችላል።
አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ ስራ መሰራቱን ገልጸው፤ የፖሊስ ሠራዊት አባላትን በማሰማራት ከክልል እና ከፌደራል የፀጥታና አካላት ጋር በመቀናጀት የፀጥታ ማስከበር ሥራ እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል።
የቤተክርስቲያኗ አባቶች በበኩላቸው የመስቀል ደመራ በዓል አከባበርን በተመለከተ የፀጥታ አካላትን ጨምሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር ባካሄዷቸው መድረኮች ሕብረተሰቡ የበዓሉ ባለቤት ሆኖ በዓሉን በድምቀት እንዲከበር የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል።
ዘንድሮ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዙ የመኪና ማለፊያ እና የእንግዶች መግቢያ ባጅ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!