ኢትዮጵያ እየተካሄደ በሚገኘው በአፍሪካ የማዕድን ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በአውስትራሊያ እየተካሄደ በሚገኘው በአፍሪካ የማዕድን ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡
በጉባዔው የማዕድን ሚኒስትር ዴዔታ ሚሊዮን ማቲዎስ የታደሙ ሲሆን ÷ የኢትዮጵያ የማዕድን ሃብትና የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ማብራራታቸው ተገልጿል።
ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በወርቅ ፍለጋና ምርት፣ በነዳጅና በተፈጥሮ ጋዝ ልማት ፣ በማዳበሪያ ምርትና በሌሎችም ዘርፎች እንዲሰማሩ ሚኒስትር ዴዔታው ጥሪ ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በዘርፉ ለሚሰማሩ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች መንግስት ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚያደርግም ማረጋገጣቸው ተጠቁሟል።