ሕብረተሰቡ የመረዳዳት ባህሉን አጠናክሮ ሊያስቀጥል ይገባል – አቶ አረጋ ከበደ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ህብረተሰቡ እርስ በእርስ የመረዳዳት ባህሉን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ።
”የበጎነት ቀን”ን ምክንያት በማድረግ በባህር ዳር ከተማ ደጋፊ ለሌላቸው 230 ወገኖች ዛሬ ድጋፍ ተደርጓል።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ እንደተናገሩት÷ ከተረፈ ሳይሆን ካለው አካፍሎ ማደር የበጎ ተግባር አንዱ መገለጫ ነው።
የበጎነት ቀን ሲከበርም ለተቸገሩ ወገኖች በማካፈል የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህላችንን የምናጎለብትበት ዕለት ነው ብለዋል።
“መሰል በጎ ተግባራት በህብረተሰቡ ዘንድ ይበልጥ እየተበራከተ እንዲመጣና የቆየ የመተሳሰብ ባህላችን እያደገ እንዲሄድ ያስችላል” ሲሉም ገልጸዋል።
ከተለያዩ ተቋማትና በጎ ፈቃደኞች በተሰበሰበ ሃብት ጧሪ ለሌላቸው፣ አቅመ ደካማ ወገኖችና ህፃናት የተደረገው ድጋፍ የሚበረታታ እንደሆነም መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡