በጋምቤላ ክልል 13 አመራሮች ከኃላፊነታቸው ተነሱ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር ምክንያት በማድረግ በተካሄደ ግምገማ 13 አመራሮች ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ አስታወቁ፡፡
እንዲሁም 55 አመራሮች አዲስና የሽግሽግ ሹመት መሰጠቱን ነው አቶ ኡሞድ ያስታወቁት፡፡
ሙሉ በሙሉ ከኃላፊነታቸው የተነሱት አመራሮች በብልሹ አሰራር፣ በአፈፃፀማቸውና በፀጥታ ችግር ክፍተት የታየባቸው ናቸው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
አዲስና በሽግሽግ ወደ ሹመት የመጡ አመራሮች የክልሉን ህዝብ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ይፈታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡
በክልል ማዕከል የተጀመረው አመራሩን የማጥራት ተግባር በቀጣይ በዞንና በወረዳ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
ህዝቡ ለክልሉ ሰላምና ልማት ከዚህ በፊት ሲያደርግ እንደነበረው ሁሉ አሁንም ከመንግሥት ጎን በመሆን የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!