Fana: At a Speed of Life!

የዘመን መለወጫ በዓላት ወንድማማችነትን የሚያጎለብቱ የጋራ ሃብቶች ናቸው – አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተከበሩ የዘመን መለወጫ በዓላት አንድነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን ያሳዩ ድንቅ የጋራ ሃብቶቻችን ናቸው አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ።
የጎፋ ዞን ሕዝብ የዘመን መለወጫ የጎፋ “ጋዜ ማስቃላ” እና የኦይዳ “ዮኦ ማስቃላ” በዓላት በሳውላ ከተማ ተከብረዋል፡፡
አቶ ጥላሁን በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በሀገረ መንግሥት ግንባታ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከተው የጎፋና የኦይዳ ሕዝብ ደግ፣ ፍትሕና እኩልነትን የሚያረጋግጥ የዳኝነት ሥርዓት አለው፡፡
የ”ጋዜ ማስቃላ” እና “ዮኦ ማስቃላ” በዓላት የብዝኃነት፣ የመቻቻልና የአንድነት ተምሳሌት ለሆነው የጎፋ ዞን ሕዝብ የአዲስ ዓመት የብሩህ ዘመን ማብሰሪያ እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።
በዓላቱ በርካታ ችግሮችን ተቋቁመን የሕዳሴ ግድብን በኢትዮጵያዊያን የተደመረ አቅምና የዓላማ ጽናት በስኬት ባጠናቀቅንበት ወቅት የሚከበሩ መሆኑ ልዩ ያደርጋቸዋል ነው ያሉት፡፡
የ”ጋዜ ማስቃላ” እና የ”ዮኦ ማስቃላ” በዓላት ሰላምና መቻቻልን፣ ሕብረትና ትብብርን፣ ወንድማማችነትና አንድነትን የሚያጠናክሩ እንዲሁም የመተሳሰብ ተግባራትን የሚያጎለብቱ እሴቶችን ያቀፉ ናቸው፡፡
ከቂምና ቁርሾ ይልቅ ሰላምን፣ ከመገፋፋት ይልቅ ሕብረትና አንድነትን የሚያጸኑ አሻጋሪ እሴቶች እንዳሏቸውም ርዕሰ መስተዳድሩ አውስተዋል፡፡
ሰላማችን ለማደፍረስ የሚፈልጉ የሴራ፣ የፈጠራና የባንዳ ትርክትን በማጥፋት የሕልውናችን መሰረት የሆነውን አንድነታችንን ጸንቶ እንዲቀጥል መስራት ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.