ዩ ኤን ዲፒ ኢትዮጵያን ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት ገለጸ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (ዩ ኤን ዲ ፒ) በኢትዮጵያ ያለውን የሰላም ግንባታ ሂደት ለመደገፍ ቁርጠኛ ነው ሲሉ የድርጅቱ ሀላፊ አቺም ሽታይነር ተናገሩ።
በኒውዮርክ ከ78ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር የተወያዩት ኃላፊው፥ ዩ ኤን ዲ ፒ ከኢትዮጵያ ጋር በሁሉም ሁኔታዎች የረጅም ጊዜ አጋር መሆኑን ጠቁመዋል።
ከመልሶ ግንባታ እና መልሶ ማቋቋም መርሃ ግብሮች በተጨማሪ ዩ ኤን ዲ ፒ የኢትዮጵያን አስደናቂ የእድገት ግስጋሴ ለማስቀጠል ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ዩ ኤን ዲ ፒ እስካሁን ላደረገው ድጋፍ አድንቀው በመንግስትና በልማት አጋሮች መካከል የተቀናጀ ጥረት እንዲደረግ ጠይቀዋል።
አቶ ደመቀ በሌሎች የልማት መርሐ ግብሮች ዙሪያም ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!