Fana: At a Speed of Life!

ፖላንድ የመጀመሪያዋን የኒውክሌር ማብላያ ማዕከል ልትገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፖላንድ መንግስት በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን የኒውክሌር ማብላያ ማዕከል ለመገንባት ከአሜሪካ ኩባንያዎች ጋር ተፈራርሟል፡፡

ዌስትንግሃውስ ኤሌክትሪክ እና ቤችቴል የተባሉ ሁለት የአሜሪካ ኩባንያዎች ናቸው በፖላንድ የመጀመሪያውን የኒውክሌር ማብላያ ማዕከል ለመገንባት የተፈራረሙት፡፡

በፖላንድ በተካሄደው የፊርማ ሥነ ሥርዓት ላይ የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማቴዎስ ሞራዊኪ እና በፖላንድ የአሜሪካ አምባሳደር ማርክ ብሬዚንስኪ ተገኝተዋል፡፡

በስምምነቱ መሰረት ኩባንያዎች በአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ 3 የኒውክሌር ማብላያ ማዕከላትን ለመገንባትና ለሀገር ውስጥ ሰራተኞች የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ መስማማታቸው ተገልጿል፡፡

ቀደም ሲል ፖላንድ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት(ኔቶ)ኒውክሌር መጋራት ፕሮግራምን ለመቀላቀል ፍላጎት አሳይታ እንደነበር አርቲ በዘገባው አስታውሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.