Fana: At a Speed of Life!

የጨልጨል መስኖ ልማት ፕሮጀክት በ2018 በጀት ዓመት ይጠናቀቃል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ5 ነጥብ 15 ቢሊየን ብር ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው የጨልጨል መስኖ ልማት ፕሮጀክት በ2018 በጀት ዓመት መጨረሻ ላይ እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ፡፡

የጨልጨል መስኖ ልማት ፕሮጀክት በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ባለቤትነት በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ባሌ ዞን በራይቱ እና በጊኒር ወረዳ የግድብና ተያያዥ ስራዎች ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ፕሮጀክቱ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ 4 ሺህ 146 ሄክታር መሬት በማልማት ከ9 ሺህ በላይ አርብቶአደሮች እና ከፊል-አርብቶአደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡

በጊኒርና ራይቱ ወረዳዎች አዋሳኝ ቦታ የዌብ ወንዝ ገባር በሆነው ጨልጨል ወንዝ ላይ እየተካሄደ የሚገኘው ግድብ ከፍታው 46 ነጥብ 5 ሜትር፣ ርዝመቱ 681 ሜትር እንዲሁም 114 ሜትር ከፍታ ያለው የመስኖ ውሃ ማስወጪያ ማማ አለው።

ግደቡ 50 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን 1 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ውሃ ወደ ኋላ በመተኛት 341 ነጥብ 8 ሄክታር መሬት በውሃ እንደሚሸፍን ነው የተገለፀው፡፡

በታህሳስ 2012 ዓ.ም የተጀመረው ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በራይቱ ወረዳ በዓመት ውስጥ ከ 3 ጊዜ በላይ ማምረት ያስችላል ተብሏል፡፡

ፕሮጀክቱን በ2018 በጀት ዓመት መጨረሻ ለማጠናቀቅ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.