Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ282 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኩርሙክ ወረዳ ከ282 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ለማካሄድ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡

የመሠረት ድንጋዩን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) አስቀምጠዋል።

ፕሮጀክቱ በወረዳው ሆራአዛብ ከተማና አካባቢው ቀበሌዎች የሚገኙ 47 ሺህ 317 የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.