Fana: At a Speed of Life!

ብልጽግና ፓርቲ ታሪክን ወደ ሀብት፥ ቅርስን ወደ እሴት የቀየረ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ብልጽግና ፓርቲ ታሪክን ወደ ሀብት፥ ቅርስን ወደ እሴት የቀየረ ነው አሉ።

ብልጽግና ፓርቲ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደርበት የምርጫ ምልክት ‘የስንዴ ነዶ’ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡

ፓርቲው “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ የማኒፌስቶ እና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ይፋ ማድረጊያ መድረክ በዋና ጽ/ቤቱ አካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት እና የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አደም ፋራህን ጨምሮ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በመርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ፓርቲው ታሪክን ወደ ሀብት፥ ቅርስን ወደ እሴት የቀየረ ነው ብለዋል።

ብልጽግና ፓርቲ ከ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኋላ በኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ዘርፎች ላይ ባከናወናቸው ዘርፈ ብዙ ለውጦች ውስጥ ኢትዮጵያ ትገኛለች ነው ያሉት።

በዚህም በዲጂታል ኢትዮጵያ፣ በዲጂታል ፋይናንስ፣ በዲጂታል አገልግሎት እንዲሁም ሀገሪቱን ከዕዳ ወደ ምንዳ የማሻገር ስራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል።

በማህበራዊ መስተጋብሮች፣ በህዝቦች መካከል ትስስር የመፍጠር ህዝባዊና ባህላዊ በዓላት እንዲጠናከሩ መደረጉን አንስተው፤ ይህም ኢትዮጵያ አቀርቅራ እንደማትቀር አሳይቷል፣ ታሪክም ተቀይሯል ብለዋል።

በሰለሞን በየነ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.