የኢትዮጵያና ታንዛኒያ ወታደራዊ ግንኙነትን ለማጠናከር ያለመ ምክክር ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ በመካከላቸው ያለውን ወታደራዊ ግንኙነት በይበልጥ ለማጠናከር በሚያስችላው አግባብ ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡
116ኛውን የሠራዊት ቀን ለመታደም እና በዘርፉ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ወታደራዊ ግንኙነት ለማጠናከር አዲስ አበባ የገቡት የታንዛኒያ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል ጃኮፕ ጆን ከጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር ተወያይዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ግንኙነት ለማጠናከር እና በስልጠና ጉዳዮች በጋራ ለመስራት በሚችሉባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ መምከራቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!