Fana: At a Speed of Life!

የዓለም የቱሪዝም ቀንን አስመልክቶ ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ለ44ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ36ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም ቱሪዝም ቀን አስመልክቶ ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር)÷ ኢትዮጵያ የቱሪዝም መስራች ሀገር መሆኗን አንስተዋል፡፡

የዘንድሮ የቱሪዝም ቀን አዲስ አበባ የዓለም የቱሪዝም ከተሞች ፌዴሬሽን አባል የሆነችበት ፣ የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር እና የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡበት መሆኑ ለየት ያደርገዋል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የዘንድሮው የቱሪዝም ቀን ቱሪዝም በኢትዮጵያ ከማህበራዊ ዘርፍ ወጥቶ ወደ ኢኮኖሚ ዘርፍ በተለወጠበት ወቅት መከበሩ ለየት እንደሚያደርገው ሚኒስትሯ ገልፀዋል፡፡

በፈቲያ አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.