Fana: At a Speed of Life!

ኢጋድ የሱዳን የተኩስ አቁም ንግግርን በጂዳ ሊያስተባብር መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢጋድ የሱዳን የሰብአዊ ተኩስ አቁም ንግግርን በሳዑዲ አረቢያ ጂዳ ሊያስተባብር መሆኑ ተገለጸ፡፡
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) የሱዳንን ውይይት ከአፍሪካ ህብረት፣ ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት እና አሜሪካ ጋር በጋራ ለማመቻቸት የኢጋድ የመሪዎች ምክር ቤትን በመወከል በጂዳ እንደሚገኙ ተገልጿል።
ንግግሩ በሱዳን ዘላቂ የሆነ ሰብአዊ የተኩስ አቁምን ለማሳካት ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
ኢጋድ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመሆን የሱዳን ባለድርሻ አካላት የሚያደርጉትን ሁሉን አቀፍ ፖለቲካዊ ውይይት በሱዳናውያን ባለቤትነት እና መሪነት በኢጋድ ቀጣና እንደሚካሄድም ገልጿል።
ኢጋድ የሱዳን ህዝብ ዘላቂ ሰላምና ፖለቲካዊ መረጋጋት እንዲያገኝ ቆራጥ አቋም እያሳዩ ካሉ የሱዳን ወዳጆች ጋር በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ እንደሚሰራ መግለፁን የኢጋድ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.