የኢትዮጵያንና የግሪክን ግንኙነት በይበልጥ ለማሣደግ በሚቻልበት ሁኔታ ምክክር ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን እና የግሪክን የቆየ ታሪካዊ ግኝኙነት በይበልጥ ማሣደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደረገ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ ከግሪክ አምባሳደር አና ፋሩ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
አምባሳደር ምሥጋኑ በዚህ ወቅት የሁለቱን ሀገራት የቆየ የሕዝብ ለሕዝብ ታሪካዊ ግንኙነት የሀገራቱን የጋራ ተጠቃሚነት ወደሚያረጋግጥ ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት ማሣደግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
አምባሳደር አና ፋሩ በበኩላቸው÷ የሀገራቱን የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት በይበልጥ ለማሣደግ እና ለማስፋት በጋራ መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት በይበልጥ ለማሣደግ እንዲቻልም አምባሳደር ምሥጋኑ ግሪክን እንዲጎበኙ ግብዣ ቀርቦላቸዋል፡፡
አምባሳደር ምሥጋኑ የቀረበላቸው ጥሪ መቀበላቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡