Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በአረብ ሀገራት የምታደርገውን ዲፕሎማሲያዊ ግፊት መቀጠሏ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአረብ ሀገራት በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እየጠየቁ ባሉበት ወቅት አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግፊቷን አጠናክራ መቀጠሏ ተገልጿል።
 
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ወደ ቱርክ አቅንተዋል።
 
ሚኒስትሩ ከቀጣናው ሀገራት መሪዎች ጋር ሰብአዊ ተኩስ አቁም እንዲደረስ ሲሰሩ እንደቆዩ በመጥቀስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንም በጉዳዩ ላይ የተወሰነ መሻሻል እንዳለ አስተያየት መስጠታቸው ተጠቁሟል፡፡
 
የአረብ ሀገራት በጋዛ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ቢጠይቁም አሜሪካ በበኩሏ ይህ ለሃማስ እንደገና እንዲደራጅ ዕድል ይሰጠዋል ስትል አስጠንቅቃለች፡፡
 
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እስከ አሁን ወደ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚጠጉ የተፈናቀሉ ሰዎች በጋዛ መኖራቸውን ገልጿል፡፡
 
በደቡብ ያሉት መጠለያዎች ከአቅም በላይ ሰዎች በመያዛቸው አዲስ የሚመጡ ተፈናቃዮችን አልቀበልም ማለቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
 
ሃማስ በፈረንጆቹ ጥቅምት 7 በእስራኤል ላይ ጥቃት ካደረሰ በኋላ እስራኤል በጋዛ ላይ አጸፋዊ ምላሽ መስጠት የጀመረች ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ከ9 ሺህ 400 በላይ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን ዘገባው አመላክቷል።
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.