የወጣቱን ስብዕና ለመቅረጽና ሀገርን ለማሻገር ያለመ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “የለውጥ ትውልድ” የተሰኘ የወጣቱን ስብዕና ለመቅረጽና ሀገርን ለማሻገር ያለመ ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ፕሮጀክቱ ቅን ቢዝነስ ግሩፕ ከተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር የተሰናዳ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በቀጣይ 8 አመታትም በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የሚተገበር መሆኑን እና 20 ሚሊዮን ወጣቶችን ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱን ገልጸዋል።
የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማው በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ ወጣቶች ስልጠና በመስጠት ስብዕናቸው የታነጸ፣ ህይወታቸው የተለወጠ፣ ለሀገራቸውና ለወገናቸው ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ወጣቶችን ማብቃት መሆኑን አመላክተዋል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያን ወደ ቀደመ ከፍታዋ ለመመለስ በሚደረገው ጥረት በባለቤትነት ስሜት የሚረባረቡ ወጣቶችን ለማፍራት እንደሚሰራ መግለጻቸውን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ለትውልድ ወሳኝ የሆነው ይህ ሀገራዊ ፕሮጀክት ስኬታማ እንዲሆን የክልልና የከተማ አስተዳደር የስራ አስፈፃሚ አካላት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!