Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድና ኢትዮ ቴሌኮም 12 በመቶ ዕድገት አስመዝግበዋል – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትራንስፖርትና ኮሙኒኬሽን ዘርፎች ከፍተኛ ዕድገት ማስመዝገባቸውን ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በማብራሪያና ምላሻቸውም በአጠቃላይ የአገልግሎት ዘርፉ ያስመዘገበው ዕድገት 7 ነጥብ 9 በመቶ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

የአገልግሎት ዘርፉ ዕድገት ጥሩ ቢሆንም የኢትዮጵያ ዓየር መንገድና ኢትዮ ቴሌኮም ያስመዘገቡት 12 በመቶ ገደማ ዕድገት ስኬታማ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የሆቴል ዘርፉ ከ10 በመቶ በላይ ማደጉን ጠቁመው በዚህ ዓመት በይበልጥ ዕድገት ያስመዘግባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቅሰዋል።

ለዚህም አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት ኢትዮጵያ በቱሪዝሙ ዘርፍ ከፍተኛ መነቃቃት ላይ እንደምትገኝ መግለጻቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡

የሀገር ውስጥ ቱሪዝም እየሰፋ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በአጠቃላይ ኢኮኖሚያችን ባሰብነው ልክ እንደሚያድግ ይጠበቃል ብለዋል ለምክር ቤት አባላት በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.