ምክር ቤቱ የቀረበለትን ሞሽን አፀደቀ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክር ቤቱ መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም በፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የቀረበውን የ2016 የመንግስት የትኩረት አቅጣጫ ሞሽን በመሉ ድምፅ አፅድቋ፡፡
6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ዛሬ ተካሄዷል ፡፡
በጉባኤው በፕሬዚዳንቷ የቀረበውን ሞሽን መነሻ በማድረግ ከምክር ቤት አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ተሠጥቶባቸዋል፡፡
በመጨረሻም ምክር ቤቱ የቀረበለትን ሞሽን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡