በክልሉ ከአበባ እና አትክልት ምርቶች ከ8 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል ተባለ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በመኸር ወቅት ከአበባ እና አትክልት ዘርፍ ከ8 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ ተመላከተ፡፡
በዘርፉ በምርት ከተሸፈነው 35 ሺህ 195 ሔክታር ከ8 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ማስረሻ በላቸው ገልጸዋል፡፡
ለዘርፉ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑንም ነው ለኢዜአ የተናገሩት፡፡
እስካሁን ከ4 ሺህ 868 ሔክታር በላይ በሆነ መሬት የሚገኝ ሰብል መሰብሰቡን እና ከዚህም ከ889 ሺህ በላይ ኩንታል ምርት መገኘቱን ጠቅሰዋል፡፡
አሁን እየጣለ ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የደረሱ የሆርቲካልቸር ምርቶችን እንዳያበላሽ በተደራጀ መልኩ ፈጥኖ መሰብሰብ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡