Fana: At a Speed of Life!

የኢጋድ 2ኛው የተቀናጀ የፍልሰተኞች ጉዳይ ምላሽ የሕግ ማዕቀፍን የተመለከተ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 5 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ሁለተኛው የተቀናጀ የፍልሰተኞች ጉዳይ ምላሽ የህግ ማዕቀፍን የተመለከተ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።

ኢጋድ የመጀመሪያውን የፍልሰተኞች ጉዳይ ምላሽ የህግ ማዕቀፍ ከፈረንጆቹ 2015 እስከ 2020 ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል።

የኢጋድ የጤና እና ማህበራዊ ልማት ዳይሬክተር ፈቲሃ አልዋን የፍልሰተኞች ጉዳይ የተወሳሰበ በመሆኑ የተቀናጀ ጥረትን ከመላው ዓለም ይፈልጋል ነው ብለዋል።

ቀጠናው የፍልሰተኞች ጉዳይ ላይ ካለበት ችግር እንዲወጣ ሁለተኛው የተቀናጀ የህግ ማዕቀፍ ወሳኝነት እንዳለውም ገልጸዋል።

በፍትህ ሚኒስቴር የብሄራዊ ትብብር ጥምረት የጽህፈት ቤት ሃላፊ አብርሃም አያሌው የኢትዮጵያ መንግስት የፍልሰተኞችን ጉዳይ በተቀናጀ መልኩ ለመምራት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የፍልሰተኞች ጉዳይን በተመለከተ ኢትዮጵያ የተለያዩ የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ጭምር እየሰራች መሆኑንም ነው የገለጹት።

ሆኖም ቀጠናውን እየፈተነ የሚገኘውን ህገወጥ ስደትን ለመከላከል ሃገራት በጋራ እንዲሰሩ የህግ ማዕቀፉ ወሳኝነት ይኖረዋልም ብለዋል አቶ አብርሃም።

ሁለተኛው የተቀናጀ የፍልሰተኞች ጉዳይ ምላሽ የህግ ማዕቀፍ ከፈረንጆቹ 2024 እስከ 2028 የሚተገበር ሲሆን የፍልሰተኞችን ህይወት በማሻሻል፣ በጤና አጠበባቅ እና በትምህርት ተደራሽነት ላይ ትኩረት ይሰጣል።

የህግ ማዕቀፉ የኢጋድ አባላት ሃገራት በፍልሰተኞች ጉዳይ የበለጠ ተቀራርበው መስራት የሚያስችላቸው መሆኑ ተገልጿል።

በኢጋድ አባል ሃገራት ከ3 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ፍልሰተኞች መኖራቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በምስክር ስናፍቅ

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.