Fana: At a Speed of Life!

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በጂ.ኤስ.ኤም እና ኤምፔሳ አገልግሎቶች ትልቅ ምዕራፍ አስመዝቤያለሁ አለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በግማሽ ዓመት አፈፃፀሙ ጠንካራ የንግድ እንቅስቃሴን በማከናወንእ በጂ.ኤስ.ኤም እና ኤምፔሳ አገልግሎቶች ትልቅ ምዕራፍ እያስመዘገበ መሆኑን ገለፀ።

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ በቴሌኮም አገልግሎት ከተሰማራ ጊዜ አንስቶ ፈጣን አስተማማኝ ጥራት ያለው የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎትን ለማስፋፋት እየሰራ ነው ያሉት አዲሱ የሳፋሪኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ዊም ቫንሄለፑት ናቸው፡፡

አሁን ላይ ሳፋሪኮም ከ4 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉትም ተናግረዋል።

ኩባንያው የገነባቸው የቴሌኮም ማማዎች 2 ሺህ 57 መድረሳቸው ገልጸው፥ በየወሩም 150 ማማዎች እየተገነቡ መሆናቸውን አመልክተዋል።

ከቴሌኮም አገልግሎት ባለፈ በፋይናንስ ዘርፉ ለመሰማራት ባለፈው ነሐሴ ወር ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ የወሰደው ኤምፔሳ ደግሞ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ደንበኞች ማፍራቱንና ከ12 የሀገር ቤት ባንኮች ጋርም አብሮ እየሰራ እንደሆነ ተገልጿል።

በትዕግስት አስማማው

#Ethiopia #Safaricom

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.