ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)በሲዳማ ክልል የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ፕሮጀክትን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ከዓለም ባንክ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በሲዳማ ክልል በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ፕሮጀክት ድጋፍ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ጎበኙ።
በጉብኝቱ ላይ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር)ን ጨምሮ በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሱዳንና የደቡብ ሱዳን ካንትሪ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን እንዲሁም የሲዳማ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የፕሮጀክቱ አስፈጻሚ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
አመራሮቹ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ዘርፍ የልማት ሥራዎችን መጎብኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በክልሉ በዳሌ ወረዳ ደቡብ መሰንቀላ ቀበሌ የሚገኘውን የወጣቶች ዶሮ እርባታ ማዕከል በመጎብኘት በልማቱ የተሳተፉ ወጣቶችን አበረታተዋል።