Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በ3ኛው የአፍሪካ ዓለም አቀፍ የሕብረተሰብ ጤና ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በዛምቢያ ሉሳካ እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው የአፍሪካ ዓለም አቀፍ የህብረተሰብ ጤና ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

በአፍሪካ በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል እና በዛምቢያ ጤና ሚኒስቴር የተዘጋጀው 3ኛው የአፍሪካ ዓለም አቀፍ የህብረተሰብ ጤና ጉባዔ በሉሳካ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በመድረኩ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እየተሳተፉ መሆኑን ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

የአፍሪካ መሪዎች፣ የዘርፉ ተመራማሪዎች፣ ሕግ አውጪዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም በጉባዔው ተሳትፈዋል፡፡

ጉባዔው በአፍሪካ የሚስተዋሉ በሽታዎችን መከላከል የሚያስችል አቅምን በዘላቂነት መገንባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየመከረ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.