Fana: At a Speed of Life!

ከሚሽኑ ከዳያስፖራዎች ጋር የሚያደርገው የበይነ መረብ ስብሰባ በፈረንጆቹ ታሕሳስ 9 ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በውጭ ሀገራት ከሚትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር የሚያደርገው የበይነ መረብ ስብሰባ በፈረንጆቹ የፊታችን ታሕሳስ 9 ቀን እንደሚጀመር አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ሰኔ 20 ቀን 2015 ዓ.ም በውጭ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በበይነ መረብ ስብሰባ ለማድረግ ጥሪ ማቅረቡ የሚታወስ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ኮሚሽኑ ይህንን ተግባር በተሻለ ዝግጅትና አቀራረብ ማከናወን አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘው ስብሰባውን ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ ይታወቃል፡

ኮሚሽኑ አሁን ላይ ተገቢ ቅድመ-ዝግጅት በማድረግ በፈረንጆቹ ታሕሳስ 9 ቀን 2023 የመጀመሪያውን ዙር የበይነ-መረብ ስብሰባ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ በሚያሰናዳው የበይነ-መረብ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ከዚህ ቀደም ተመዝግበው በትዕግስት ሲጠባበቁ ለነበሩ ወገኖች ምስጋና አቅርቦ፤ በስብሰባው ላይ መሳተፍ የሚያስችለውን ሊንክ (ዙም ሊንክ) ለተሳታፊዎች በኢሜል አድራሻ እንደሚልክም አስታውቋል፡፡

የመጀመሪያው ዙር ስብሰባ የሚደረገውም በአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ውስጥ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር መሆኑ ተገልጿል፡፡

የበይነ መረብ ስብሰባውም በፈረንጆቹ የፊታችን ታሕሳስ 9 ቀን ከ9 ሰዓት (3 PM ወይም 15:00) ጀምሮ እንደሚከናወን የኮሚሽ መረጃ ያመላክታል፡፡

ስለሆነም በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በኢትዮጵያ የወደፊትዕጣ ፈንታ ላይ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል ተብሎ በሚጠበቀው ሀገራዊ ምክክር ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በሌላ በኩል ከአሁን በፊት በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ ያልተመዘገቡ እና አሁን መሳተፍ የሚሹ ወገኖች በሊንክ https://forms.gle/1QgddMx6XFMeDCiY7 መመዝገብ የሚችሉ ሲሆን÷ በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ የሚያስችለው ሊንክም በኢሜል አድራሻቸው የሚላክ ይሆናል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.